AMN – መጋቢት 7/2017 ዓ.ም
መንግስት የዜጎችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የጀመረው የምግብ ዋስትና ፕሮግራም የኢኮኖሚ ሪፎርሙን ተከትሎ የመጣ መሆኑን በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ሥራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ ገለጹ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የስራና ክህሎት ቢሮ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ 154 ሺህ 923 ዜጎችን በሴፍትኔት የስራ ፕሮጀክት ተጠቃሚ ለማድረግ ከተረጂነት ወደ ምርታማነት ለማሸጋገር የሚያስችል መርሀ ግብር አካሂዷል።
በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማም “ከተረጂነት ወደ አምራችነት” በሚል መሪ ሀሳብ ከ16ሺህ አምስት መቶ በላይ ዜጎች ተጠቃሚ የሚሆኑበት ፕሮግራም ይፋ ተደርጓል።
መርሃ ግብሩን ያስጀመሩት በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ሥራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ፣ የሥራ እድሉ ተጠቃሚዎች በርትታችሁ በመሥራት ራሳችሁን እና ከተማዋን መቀየር አለባችሁ በማለት አሳስበዋል።
በአለሙ ኢላላ