ከኢትዮጵያ አያሌ የቱሪስት ሀብቶች መካከል በጥንታዊ በግምብ የተከበበችው ታሪካዊቷ የሀረር ከተማ ልትጎበኝ የሚገባት መዳረሻ ናት።

You are currently viewing ከኢትዮጵያ አያሌ የቱሪስት ሀብቶች መካከል በጥንታዊ በግምብ የተከበበችው ታሪካዊቷ የሀረር ከተማ ልትጎበኝ የሚገባት መዳረሻ ናት።

በምስራቁ የሀገራችን ክፍል የምትገኘው ሀረር ከ13ኛው እስከ 16ኛው ክፍለ ዘመን በተገነቡ ጥንታዊ ግምቦች የተከበበች ፣ በእስልምና የተከበረች፣ በታሪክ እና በባህል ሀብታም የሆነች ከተማ ናት።

በግምቦቹ ውስጥ 82 መስጊዶች እና 102 የእስልምና ቅዱሳት ስፍራዎች ይገኛሉ። ይኽም በተወሰነ ቦታ ከፍተኛ የመስጊድ ቁጥር ካለባቸው ቦታዎች አንዷ ያደርጋታል።

የሀረር ደማቅ ገበያ እና ልዩ የሥነሕንፃ መልክ በምዕተ አመታት የዘለቀውን የነበራትን የምስራቅ አፍሪካ የገበያ ማዕከልነት የሚያንፀባርቅ ነው። ይኽን የባሕል ዋጋዋን እውቅና በመስጠትም ዩኔስኮ እ.ኤ.አ ከ2006 ጀምሮ ጀጎልን በአለም ቅርስነት መዝግቧል። ጎብኝዎች በዘመኑ በሀረር የነበረውነ‍እ የፈረንሳይ ገጣሚ የሚዘክረውን የአርተር ራምቦ ሙዚየምን የመሰሉ ቦታዎችን መመልከት ይችላሉ።

ጀምበር ስትጠልቅም የሀረር እጅግ ታዋቂ የሆነው የጅብ ምገባ ክዋኔ በአስደናቂ አኳኋን ይታያል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review