ማይናማር በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 53 ኢትዮጵያውያን ወደ አገራቸው ተመለሱ

You are currently viewing ማይናማር በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 53 ኢትዮጵያውያን ወደ አገራቸው ተመለሱ

AMN- መጋቢት 8/2017 ዓ.ም

መንግሥት በዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲ ትኩረት ሰጥቶ በመንቀሳቀስ በማይናማር በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 53 ኢትዮጵያውያን ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ማድረጉን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

ከማይናማር እገታ ወጥተው ታይላንድ ወታደራዊ ካምፕ የነበሩ ሲሆን ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር በመተባበር እና በአካባቢው ከሚገኙ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ጋር በመነጋገር ትናንት 23 ዜጎችን እንዲሁም ዛሬ ሰኞ ደግሞ 30 ዜጎችን በአጠቃላይ በካምፑ የነበሩትን 53 ዜጎች እንዲመለሱ ማድረግ መቻሉን ከሚኒስቴሩ የተገኘ መረጃ ያመላክታል።

እስካሁን ከማይናማር እገታ ወጥተው ታይላንድ ወታደራዊ ካምፕ የነበሩ በመጀመሪያውና ሁለተኛው ዙር በጠቅላላው 130 ዜጎችን መመለስ ተችሏል።

መንግሥት በድጋሚ ሕብረተሰቡ በሕገ ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎች ሀሰተኛ ቅስቀሳ ተታሎ የሥራ ስምሪት ውል ወደ አልተፈጸመባቸው አገራት ከሚደረጉ እንቅስቃሴዎች እንዲቆጠብ አሳስቧል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review