AMN – መጋቢት 9/2017 ዓ.ም
ምሽቱን እስራኤል በጋዛ ባካሄደችው የአየር ጥቃት በትንሹ 330 ሰዎች መሞታቸው ተነግሯል፡፡
በሀማስ እና እስራኤል መካከል የተደረገው የተኩስ አቁም ስምምነት ወደ ተግባር ከገባበት ጥር 17 ቀን 2025 ወዲህ የዚህ አይነቱ መጠነ ሠፊ የአየር ላይ ጥቃት በጋዛ ሲፈፀም የመጀመሪያው ነው፡፡
ሀማስ ታጋቾችን ባለመልቀቅ እና የተኩስ አቁም ለማራዘም የቀረበውን ምክረ ሀሳብ ውድቅ በማድረጉ እስራኤል በሀማስ ላይ መውሰድ የጀመረችውን እርምጃ አጠናክራ እንደምትቀጥል የጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያምን ኔታኒያሁ ፅ/ቤት መግለፁን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
ሀማስ በበኩሉ እስራኤል በንፁሀን ላይ በምትፈፅመው እና ተኩስ አቁሙን በመቀልበሷ ተጠያቂ ልትሆን ይገባል በሚል ክስ አቅርቧል፡፡