ኢትዮጵያ የምርት ጥራትን ለማረጋገጥ እየሰራች ነው

You are currently viewing ኢትዮጵያ የምርት ጥራትን ለማረጋገጥ እየሰራች ነው

AMN – መጋቢት 10/2017

ኢትዮጵያ ለሀገር ውስጥ እና ለውጭ ሀገራት የምታቀርባቸውን ምርቶች ጥራት ለማስጠበቅ የጥራት መንደር አቋቁማ እየሰራች እንደምትገኝ ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ገልጿል።

የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ከንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ጋር በመተበባር በዓለም ለ42ኛ ጊዜ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ12ኛ ጌዜ የሚከበረውን የዓለም የሸማቾች ቀን “ጥራቱን የጠበቀ ምርት ለሸማቾች” በሚል መሪ ሀሳብ እያከበረ ይገኛል።

የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ሀላፊ ሀቢባ ሲራጅ፣ በሀገሪቱ የሸመቾችን መብት ለማስጠበቅ የሚረዳ አዋጅ ከወጣ ጀምሮ በርካታ ስራዎች ሲሰሩ መቆየታቸውን ተናግረዋል።

አምራቹ ጥራቱን የጠበቀ ምርት እንዲያቀርብ እና ሸማቹ በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲገዛ በርካታ ስራዎች መሰራታቸውንም አመልክተዋል።

በንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር የንግድና ሸማቾች ጥበቃ መሪ ስራ አስፈፃሚ አቶ ሊቁ በነበሩ በበኩላቸው፣ ኢትዮጵያ ለሀገር ውስጥ እና ለውጭ ሀገራት የምታቀርባቸውን ምርቶች ጥራት ለማስጠበቅ የጥራት መንደር አቋቁማ እየሰራች እንደምትገኝ ተናግረዋል።

በሸማቹ ማህበረሰብ ላይ የሚደርሰውን የመብት ጥሰት በመከላከል ረገድ በርካታ ስራዎች መሰራታቸውን እንደገለጹም ከአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review