ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ባለፉት 8 ወራት ከ580 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን ገለጹ

You are currently viewing ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ባለፉት 8 ወራት ከ580 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን ገለጹ

AMN-መጋቢት 11/2017 ዓ.ም

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ባለፉት ስምንት ወራት ከ580 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን ገልጸዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ማብራሪያ እና ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገቢን በተመለከተ በሰጡት ማብራሪያ፣ ባለፉት 8 ወራት ከ580 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን ተናግረዋል።

ነገር ግን መንግስት የሚሰበስበው ገቢ ከጥቅል ሀገራዊ ምርት አንፃር ከ7 በመቶ እንደማይበልጥ ያነሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ይህ መሻሻል እንደሚገባው አስገንዝበዋል።

በየአከባቢው የሚቀርቡ የልማት ጥያቄዎችን መመለስ የሚቻለው ገቢ በበቂ ሁኔታ ማሳደግ ሲቻል ብቻ እንደሆነም ነው የጠቆሙት።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review