AMN – መጋቢት 11/2017 ዓ.ም
አለም አቀፉ ኦሎምፒክ ኮሚቴ (IOC) በዛሬው እለት በግሪክ 144ኛውን ጠቅላላ ጉባኤው አድርጎ በቀጣይ 8 ዓመታት የተቋሙን ፕሬዝዳንት ምርጫ ሲያደርግ የመጀመሪያዋን ሴት ፕሬዝዳንት አድርጎ መርጧል።
ዙምባብዊቷ የ41 ዓመቷ ክርስቲ ኮቨንትሪ ጀርመናዊውን ቶማስ ባህን በመተካት ፕሬዝዳንት ሁናለች።
ከፍተኛ የማሸነፍ ግምት ተሰጥቷቸው የነበሩትን የወቅቱ የአለም አትሌቲክስ ፕሬዝዳንት ሰባስታፈቲያን ኮን በመብለጥ ትልቁን ተቋም ለመምራት ተመርጣለች።
በአንዱዓለም ስማቸው