የዓለም ንግድ ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት አባል እንድትሆን ድጋፍ እንደሚያደርጉ ገለጹ

You are currently viewing የዓለም ንግድ ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት አባል እንድትሆን ድጋፍ እንደሚያደርጉ ገለጹ

AMN-መጋቢት 12/2017 ዓ.ም

የዓለም ንግድ ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ኒኮዚ አዌላ (ዶ/ር) ኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት አባል እንድትሆን ድጋፍ እንደሚያደርጉ መግለፃቸውን የንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) ገልጸዋል፡፡

ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት መልዕክት፣ ከዓለም ንግድ ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ኒኮዚ አዌላ (ዶ/ር) ጋር በሀገሪቱ የንግድ ድርድር ሂደት ዙሪያ ፍሬያማ ውይይት ማካሄዳቸውን አመልክተዋል::

እስካሁን የተኬደበትን የሁለትዮሽ እና የባለ ብዙ ወገን ድርድሮች አፈፃፀም ለዳይሬክተሯ ማብራራታቸውን የገለጹት ሚኒስትሩ፣ በተመሳሳይ በሚቀጥሉት ጊዜያት በሚኖሩት የተናጠል እና የጋራ ውይይት ርብርብ የሚያስፈልጉ ጉዳዮችን ማንሳታቸውንም ገልጸዋል::

ዳይሬክተሯም ኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት አባል ሆና ማየት ትልቁ ውጥናቸው መሆኑን የገለጹ ሲሆን፣ የትኛውንም አይነት ድጋፍ ከማድረግ እንደማይቆጠቡ መግለፃቸውን ጠቁመዋል፡፡

በሌላ በኩል ለአፍሪካ ቡድን እና ለአባል ሀገራት የኢትዮጵያን የአባልነት ድርድር እንዲደግፉ ይፋዊ ጥሪ እንደሚያስተላልፉ መግለፃቸውንም አመላክተዋል::

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review