የኢትዮጵያ ወንዶች ብሄራዊ ቡድን የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ አምስተኛ ጨዋታውን ዛሬ እኩለ ሌሊት ከግብጽ ጋር ያደርጋል

You are currently viewing የኢትዮጵያ ወንዶች ብሄራዊ ቡድን የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ አምስተኛ ጨዋታውን ዛሬ እኩለ ሌሊት ከግብጽ ጋር ያደርጋል

AMN-መጋቢት 12/2017 ዓ.ም

በምድብ አንድ ከግብጽ፣ ቡርኪና ፋሶ፣ ጊኒ ቢሳው፣ ሴራሊዮን እና ጂቡቲ ጋር የተደለደሉት ዋልያዎቹ አራት ጨዋታዎችን አድርገው በ3 ነጥብ አምስተኛ ደረጃን ይዘዋል፡፡

ዋልያዎቹ በቡርኪና ፋሶ ሲሸነፉ ከጊኒ ቢሳው፣ ሴራሊዮን እና ጂቡቲ ጋር አቻ መለያየታቸው ይታወቃል፡፡

በመሳይ ተፈሪ የሚሰለጥነው በሄራዊ ቡድኑ ለጥቂት ቀናት በአዲስ አበባ ሲዘጋጅ ሰንብቶ ባሳለፍነው ማክሰኞ ምሽት ወደ ሞሮኮ አምርቶ ሁለት ጊዜ ልምምድ ሰርቷል፡፡

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን መስፈርትን ያሟላ ሜዳ ስለሌለው በተዋሰው የሞሮኮ ስታድዬም ነው ዛሬ ጨዋታውን የሚያደርገው፡፡

ተጋጣሚው ግብጽ ከአራት ጨዋታዎች ሶስት አሸንፋ አንድ አቻ ወጥታ ያለ ምንም ሽንፈት ምድቡን እየመራች ነው፡፡

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን የዛሬውን ጨዋታ ካሸነፈ እስከ ሁለተኛ ደረጃ ድረስ ከፍ የሚል ሲሆን፣ግብጽ ከረታች ግን መሪነቷን ታሰፋለች፡፡

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን አቡበከር ናስርን ጨምሮ 23 አባላት ያሉትን ስብስብ ይዞ ሞሮኮ ላይ ሁለት ጨዋታዎችን ለማድረግ እየተጠባበቀ ነው፡፡

በታምራት አበራ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review