የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሸነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል የመሠረታዊ ፖሊስ ስልጠና ማዕከል ግንባታ ማስጀመሪያ የመሠረት ድንጋይ በአዋሽ ሰባት ከተማ አስቀምጠዋል።
ኮሚሸነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል በሥነ-ስርዓቱ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፣ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች የትምህርት እና ስልጠና ማዕከላትን በመገንባት የኢትዮጵያን ፖሊስ ለማዘመን በርካታ ተግባራትን እያከናወነ መሆኑን ገልጸዋል።
ይህ የመሠረት ድንጋይ የማስቀመጥ ሥነ-ስርዓትም የዚሁ ማሳያ አንዱ አካል ነው ብለዋል ።
የሚገነባው የስልጠና ማዕከል በአጭር ጊዜ ውስጥ ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት ሲጀምር ለኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ብቻ ሳይሆን ለሀገሪቱ የፖሊስ ተቋማትም የፖሊስ ስልጠና መስጠት የሚያስችል መሆኑን ተናግረዋል።
ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል በአዋሽ ሰባት ማሰልጠኛ ማዕከል ስልጠና እየተከታተሉ የሚገኙ የመሠረታዊ ፖሊስ ስልጣኞችንም መጎብኘታቸውን ከኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።