ከ500 በላይ የሚሆኑ የእምነቱ ተከታዮች የተሳተፉበት የኢፍጣር መርሐ ግብር በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ተካሄዷል።
በመርሐግብሩ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አፈጉባኤ ወ/ሮ ቡዜና አልከድር ፣ የሃይማኖት አባቶች እና የተለያዩ የከተማ አስተዳደሩ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።
በመድረኩ የረመዳን ወር የእዝነትና የመልካምነት ወር መሆኑ የተገለፀ ሲሆን በዚህ ቅዱስ ወር ሕዝበ ሙስሊሙ በጋራ አብሮነቱን እንዲያጠናክር ጥሪ ቀርቧል።
ወሩን መክንያት በማድረግም የጎዳና ላይን ጨምሮ የሚከናወኑት የጋራ የአፍጥር መርሀ ግብሮችም የሕዝቦችን ወንድማማችነትና እህትማማችነትን በማጠናከር ትልቁን ሚና እየተወጡ ይገኛሉም ተብሏል።

የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈያሚ ወ/ሮ ንኢመተላህ ከበደ፣ በክፍለከተማው የተዘጋጀዉ የኢፍጣር መርሀ ግብር ይህንኑ አብሮነት ፣ መተሳሰብና መተዛዘንን ይበልጥ የሚያጠናክረዉ ነዉ ብለዋል ።
ጾምን በኢፍጣር ከወገኖቻችን ጋር በማክበራችን ከፍተኛ ደስታ ይሰማናልም ብለዋል፡፡
ወቅቱ መልካም ተግባራትን የምናከናውንበት ታላቅ ወር ነዉ ያሉት ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ ህዝበ ሙስሊሙ እንዲሁም መላዉ የህብረተሰብ ክፍል ወሩን በተምሳሌትነት እንዲወስደዉም ጠይቀዋል ።
በዚህ ተምሳሌትነትም የከተማ አስተዳደሩን የሰው ተኮር ተግባራት በማጠናከር የተጀመረውን የብልጽግና ጉዞ ከዳር ለማድረስ መላው ሕዝብ በአንድነት እንዲቆምም ጥሪያቸዉን አቅርበዋል።
በመርሐ ግብሩ ላይ ከ 500 በላይ የሚሆኑ የእምነቱ ተከታዮች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸዉ እንግዶች ተገኝተዋል ።
በአለማየሁ አዲሴ