ለ2017/18 የምርት ዘመን ግብዓት 60 ሺህ ሜትሪክ ቶን ዳፕ የአፈር ማዳበሪያ የጫነች 18ኛዋ መርከብ ጅቡቲ ወደብ ደርሳ የማራገፍ ስራ እየተሰራ እንደሚገኝ ከባህር ትራንስፖርት አገልግሎት ክፍል ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
እሰከ መጋቢት 14 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ 964 ሺ 118.1 ሜትሪክ ቶን ወይም 9 ሚሊየን 641 ሺህ 181 ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ በ18 መርከቦች ተጭኖ ጅቡቲ ወደብ መድረሱ ተገልጿል፡፡
ከዚህም ውስጥ 836 ሺህ 253.2 ሜትሪክ ቶን የአፈር ማዳበሪያ ወደ ሀገር ውስጥ የተጓጓዘ ሲሆን፣ 127 ሺህ 864.9 ሜትሪክ ቶን ደግሞ በወደብ ይገኛል፡፡
በጠቅላላው ወደ ሀገር ውስጥ ከተጓጓዘው 836 ሺህ 253.2 ሜትሪክ ቶን የአፈር ማዳበሪያ ውስጥ 705 ሺህ 073.2 ሜትሪክ ቶኑ የተጓጓዘው በድንበር ተሻጋሪ የደረቅ ጭነት ተሽከርካሪ ሲሆን፣ ቀሪው 131 ሺህ 180 ሜትሪክ ቶኑ የተጓጓዘው ደግሞ በባቡር መሆኑን ከትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ያገኘነዉ መረጃ ያመላክታል፡፡