የአሜሪካ እና የሩሲያ ውይይት በጥቁር ባሕር የተኩስ አቁም ላይ ያተኮረ ነው- ሞስኮ

You are currently viewing የአሜሪካ እና የሩሲያ ውይይት በጥቁር ባሕር የተኩስ አቁም ላይ ያተኮረ ነው- ሞስኮ

AMN- መጋቢት 15/2017 ዓ.ም

በሳዑዲ ዓረቢያ የሚካሄደው የአሜሪካ እና የሩሲያ ውይይት በጥቁር ባሕር የተኩስ አቁም ላይ ያተኮረ መሆኑን ሞስኮ ገለፀች፡፡

የአሜሪካ እና የሩሲያ ባለስልጣናት በዩክሬን የሰላም ስምምነት ላይ መድረስ በሚቻልበት ሁኔታ በሳዑዲ አረቢያ ውይይት እያደረጉ ነው፡፡

ሩሲያ በበኩሏ የዛሬው ውይይት በቀጣናው የሚቀዝፉ መርከቦች ደህንነትን ከማረጋገጥ አንፃር በጥቁር ባህር የተኩስ አቁም ላይ ትኩረት ያደረገ መሆኑን ገልፃለች፡፡

በተጨማሪም በፈረንጆቹ 2022 የተደረሰው የስንዴ ስምምነት ተግባራዊ እንዲሆን ፍላጎቷ የሚንጸባረቅበት እንደሚሆን መግለጿን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

ውይይቱ የዩክሬኑ መከላከያ ሚኒስትር ውጤታማ ሲሉ የገለጹትን በሳዑዲ አረቢያ የአሜሪካ እና የዩክሬን ባለስልጣናት ያደረጉትን የተናጠል ውይይት ተከትሎ በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡

ይሁንና በሁለቱ ሀገራት መካከል አንዳቸው በአንዳቸው ላይ የሚያደርሱት ጥቃት አሁንም እንደቀጠለ ነው፡፡

ሌሊቱን ከዩክሬን በኩል የተሰነዘሩ ጥቃቶችን ተከትሎ፣ የሩሲያ መከላከያ ሠራዊት 28 የዩክሬን ሰው አልባ አውሮፕላኖችን ማክሸፉን ገልጿል፡፡

ዩክሬን በበኩሏ፣ በሩሲያ አራት ወታደራዊ ሄሊኮፕተሮችን ማውደሟን አስታውቃለች፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review