የአውሮፓ ህብረት በኢትዮጵያ የተጀመሩ የልማት ሥራዎችን ለመደገፍ የሚያስችል የ240 ሚሊየን ዩሮ ድጋፍ ስምምነት ተፈራረመ

You are currently viewing የአውሮፓ ህብረት በኢትዮጵያ የተጀመሩ የልማት ሥራዎችን ለመደገፍ የሚያስችል የ240 ሚሊየን ዩሮ ድጋፍ ስምምነት ተፈራረመ

AMN – መጋቢት 25/2017

የአውሮፓ ህብረት በኢትዮጵያ በተለያዩ ዘርፎች የተጀመሩ የልማት ሥራዎችን ለመደገፍ የሚያስችል የ240 ሚሊየን ዩሮ የገንዘብ ድጋፍ ስምምነት ተፈራርሟል፡፡

ስምምነቱን የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሺዴ እና በኢትዮጵያ የአውሮፓ ህብረት አምባሳደር ሶፊ ፍሮም ተፈራርመዋል።

ስምምነቱ በኢትዮጵያ እና በአውሮፓ ህብረት መካከል ያለውን አጋርነት ለማጠናከር እና ዘላቂ ልማትን ለማጎልበት እንደሚያስችል ተገልጿል።

ስምምነቱ በተመረጡ ስድስት ጉዳዮች ላይ ተፈፃሚ እንደሚሆን የተገለጸ ሲሆን፣ የዴሞክራሲ ተቋማት ግንባታ፣ የሽግግር ፍትህ፣ የፆታ እኩልነት እና ማህበራዊ ትስስርን ለማጠናከር ያስችላል ተብሏል።

በስምምነቱ መሰረት ከግጭት በኋላ የመሰረታዊ የጤና አገልግሎት፣ የህክምና እና የስነ-ልቦና-ማህበራዊ ድጋፍ እንደሚሰራም ተገልጿል።

የአረንጓዴ ልማት፣ ዘላቂ የምግብ ሥርዓትን ለማጠናከር እና በቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ተቋማት የዲጂታል ክህሎት ልማት ለማጠናከር እንደሚያግዝም ተጠቅሷል።

በስምምነቱ በመታገዝ የግሉ ዘርፍ በእሴት ሰንሰለት ያለውን ሚና ለማጎልበት እንደሚሰራም መመላከቱን ኢዜአ ዘግቧል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review