አዲሱን ታሪፍ ተከትሎ የአሜሪካ የአክሲዮን ገበያ እያሽቆለቆለ ነው

You are currently viewing አዲሱን ታሪፍ ተከትሎ የአሜሪካ የአክሲዮን ገበያ እያሽቆለቆለ ነው

AMN – መጋቢት 26/2017

ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከሰሞኑ የጣሉት አዲሱ ታሪፍ የአሜሪካ የአክሲዮን ገበያው ከፈረንጆቹ 2020 ወዲህ ከፍተኛ ውድቀት አድርሶበታል ተብሏል፡፡

ትራምፕ በዓለም ሀገራት ላይ የጣሉት 10 በመቶ ዝቅተኛ የታሪፍ መጠን ዓላማው የአሜሪካ መንግስት ገቢን በከፍተኛ ሁኔታ ለመጨመር እና ዜጎች የሀገር ውስጥ ምርቶችን በብዛት እንዲጠቀሙ በማድረግ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ለማነቃቃት ታስቦ ነው፡፡

ይሁንና ውሳኔው ገና ወደ ትግበራ ሳይገባ በትላንትናው እለት በአሜሪካ የአክሲዮን ገበያው በከፍተኛ ሁኔታ ማሽቆልቆል ማሳየቱ ተሰምቷል፡፡

ትራምፕ ኢ-ፍትሀዊ የንግድ ፖሊሲን ተከትለዋል በሚል በቻይና 54 በመቶ እና በአውሮፓ ሕብረት ላይ የ20 በመቶ ታሪፍ መጣላቸው ይታወሳል፡፡
ለዚህ የትራምፕ ውሳኔ ቻይና እና የአውሮፓ ሕብረት አፀፋዊ ምላሽ እንደሚሰጡ ይጠበቃል፡፡

ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን፣ የአውሮፓ ተቋማት በአሜሪካ የሚያደርጉትን የኢንቨስትመንት ሀሳብ እንዲያቆሙ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ትራምፕ በዓለም ላይ የጣሉት አዲሱ ታሪፍ የዓለምን የሸቀጥ ዋጋ በማናር የንግድ ሥርዓትን ሊያዛባ እንደሚችል የተለየያዩ ተንታኞች ሀሳባቸውን እየገለለፁ ይገኛል፡፡

የአሜሪካ ውሳኔ ያሳሳበው የዓለም ንግድ ድርጅት በበኩሉ፣ በተያዘው ዓመት አንድ በመቶ ያህል የንግድ እንቅስቃሴ ሊቀንስ ይችላል ሲል አስታውቋል፡፡

ጉዳዩ ዓለምን እያነጋገረ ባለበት በዚህ ወቅት፣ ፕሬዚዳንት ትራምፕ አካሄዳው ትክክለኛ እንደሆነ እና የአክሲዮን ገበያው እና አሜሪካም ያድጋሉ ሲሉ ተደምጠዋል፡፡

ታሪፉን መፃረር ግን ተገቢ አይደለም ያሉት ትራምፕ፣ በዚህ ጉዳይ ላይ ለመነጋገር በራቸው ክፍት መሆኑን ገልፀዋል፡፡

አዲሱ ቀረጥ ከተጣለ በኋላ በእስያ ፓስፊክ ቀጣና የአክሲዮን ገበያው ለተከታታይ ሁለት ቀናት ውድቀት ገጥሞታል፡፡
በቀጣናው የዚህ ዓይነቱ ውድቀት ሲያጋጥም ከፈረንጆቹ 2020 ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው ተብሏል፡፡

ናይክ፣ አፕል እና ታርጌት የተሰኙ የአሜሪከ ኩባንያዎች ሽያጭ ከዘጠኝ በመቶ በላይ በመውረዱ ከፍተኛ ኪሳራ ያስተናገዱ ድርጅቶች መሆናቸውን የቢቢሲ ዘገባ አመላክተቷል፡፡

በማሬ ቃጦ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review