የኢትዮጵያን እና ኡጋንዳ ግንኙነትን የበለጠ የሚያጠናክረው አራተኛው የሚኒስትሮች የጋራ ኮሚሽን ስብሰባ ተካሄደ

You are currently viewing የኢትዮጵያን እና ኡጋንዳ ግንኙነትን የበለጠ የሚያጠናክረው አራተኛው የሚኒስትሮች የጋራ ኮሚሽን ስብሰባ ተካሄደ

AMN – መጋቢት 26/ 2017

የኢትዮጵያ እና ኡጋንዳ ግንኙነት የበለጠ ማጠናከር የሚያስችል አራተኛው የሚኒስትሮች የጋራ ኮሚሽን ስብሰባ በአዲስ አበባ ተካሂዷል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) በስብሰባው ላይ ባደረጉት ንግግር የሚኒስትሮች የጋራ ኮሚሽን ስብሰባ የሁለቱን አገራት የቆየ ግንኙነት የበለጠ በማጠናከር ረገድ ከፍተኛ ሚና ያለው መሆኑን ገልጸዋል።

ሚኒስትሩ ይኸ ስብሰባ ሁለቱ አገራት የጋራ ተጠቃሚነት መርህን መሠረት በማድረግ ግንኙነታቸውን የበለጠ እንዲያጠናክሩ የሚረዳ ነው ብለዋል።

ዶ/ር ጌዲዮን የሁለቱ አገራት ትብብር ከሁለትዮሽ ግንኙነት ባለፈ ለቀጣናው ሰላም እና መረጋጋት ወሳኝ ድርሻ እንዳለውም ገልጸዋል።

የኡጋንዳ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኦዶንጎ ጄጄ አቡበክር በበኩላቸው፤ የሁለቱ አገራት ግንኙነት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተጠናከረ መምጣቱን ተናግረዋል።

ሚኒስትሩ ኡጋንዳ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ቁርጠኛ መሆኗን ገልጸዋል።

በፖለቲካ ፣በድንበር ተሻጋሪ የውኃ ሀብት አጠቃቀም፣ በኢነርጂ፣በንግድ እና በቀጣናዊ ሰላም እና ደኀንነት ጉዳዮች ዙሪያ የመከረው የሚኒስትሮች የጋራ ኮሚሽን ስብሰባ፤ የበረራ አገልግሎት (Air Service ) ስምምነት እና ሌሎች ግንኙነቱን የበለጠ የሚያጠናክሩ ሰባት የመግባቢያ ስምምነቶችን በመፈራረም መጠናቀቁን ከዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነዉ መረጃ ያሳያል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review