በፓናል ዉይይቱ ላይ የተገኙት የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ኦርዲን በድሪ የሹዋሊድ በዓል በአለም ቅርስነት መመዝገቡ የቱሪዝም ሴክተሩን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚረዳ ነው ብለዋል።
የዘንድሮዉን የሹዋሊድ በዓል ስናከብር የለውጡን ሰባተኛ ዓመት እያሰብን የምናከብረው ነው ያሉት ርዕሰ መስተዳደሩ ባለፉት የለውጥ ዓመታት በሁሉም ዘርፎች በርካታ ለዉጦች መገኘታቸውን ገልጸዋል።
በሐረር ከተማ ኮሪደር ልማት የተፈጠረው ንቅናቄ ከተማዋ ተሞክሮ የሚቀሰምባት እንድትሆን አስችሏልም ብለዋል።
በኮሪደር ልማት የተገኙ ውጤቶችን በሌሎች መስኮች መድገም እንደሚገባም ጠቅሰዋል።
የሐረሪ ክልል ባህል እና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ አቶ ተወለዳ አብዶሽ በበኩላቸዉ የሹዋሊድ በዓል በትውልድ ቅብብሎሽ ዛሬ ላይ የደረሰ መሆኑን ጠቅሰው ለቱሪዝም ልማት አበርክቶ ያለው መሆኑን ገልጸዋል።
በተጨማሪም የህዝብ ትስስርን የሚያጠናክር መሆኑን ተናግረዋል።
በዓሉ ባህላዊ ይዘቱን ጠብቆ እንዲከበር እና ለትውልድ እንዲተላለፍ እየተሰራ ነውም ብለዋል።
በሃብታሙ ሙለታ