የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ቲክቶክን ቻይናዊ ያልሆነ ገዥ እስኪገኝ ድረስ ሊታገድ የሚችልበትን የጊዜ ገደብ ለ75 ተጨማሪ ቀናት ማራዘማቸው ተገልጿል፡፡
ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ ቲክቶክ በአሜሪካ ውስጥ ሊታገድ የሚችልበትን የጊዜ ገደብ ለሁለተኛ ጊዜ አራዝመዋል፡፡
ይህ ባለቤትነቱ በቻይናው ኩባንያ ባይትዳንስ የተያዘውን የቪዲዮ መተግበሪያ በአሜሪካ ብቻ ከ170 ሚሊዮን በላይ ተጠቃሚዎች እንዳሉት ይታወቃል።
በአሜሪካ ጉዙፋ የንግድ ተቋም ሜታ በቲክ ቶክ ተጽኖ ፈጣሪ የሆኑ ሰዎች ሜታን ሲቀላቀሉ 5ሺ ዶላር እንደሚሸልምና የቲክቶክ ተከታዮችን ደግሞ ወደ ፌስቡክ እና ኢንስታግራም ለማምጣት ፍላጎት እንዳለዉ መግለጹ የሚታወስ ነዉ፡፡
“የእኔ አስተዳደር ቲክቶክን ለማዳን በተደረገው ስምምነት ላይ በጣም ጠንክሮ እየሰራ ነው፣ እናም ትልቅ መሻሻል አድርገናል”ሲሉ ቀነ ገደቡ ሊያልቅ ጥቂት ሰዓታት ሲቀረው ዶናልድ ትራምፕ በTruth Social ላይ ተናግረዋል፡፡፣
የትራምፕ አስተዳደር የቲክቶክን ገዥ ለማግኘት እና ብዙ ባለሀብቶችን የሚያሳትፍ ድርድር እስኪፈፀም ድረስ እንዳይዘጋ ለማድረግ ስምምነት ላይ መድረሱን አጥብቀው መናገራቸው ታውቋል።
ባይት ዳንስ ከአሜሪካ መንግስት ጋር መፍትሄ ለመፈለግ እየተነጋገረ መሆኑን ሲያረጋግጥ፣ ችግሩንም ለመፍታት “ቁልፍ ጉዳዮች” እንደሚቀሩት መጠቆማቸዉን ፍራንስ 24 ዘግቧል፡፡
በወርቅነህ አቢዮ