አሜሪካ ታሪፍን እንደ መሳሪያ መጠቀም ልታቆም ይገባል ስትል ቻይና አስጠነቀቀች

You are currently viewing አሜሪካ ታሪፍን እንደ መሳሪያ መጠቀም ልታቆም ይገባል ስትል ቻይና አስጠነቀቀች

AMN – መጋቢት 27/2017 ዓ.ም

አሜሪካ ታሪፍን እንደ መሳሪያ መጠቀም ልታቆም ይገባል ስትል ቻይና አስጠነቀቀች።

አሜሪካ የጣለችውን የበቀል ታሪፍ ተከትሎ ገበያዎች ከተቀዛዙ በኋላ ዶናልድ ትራምፕ አሜሪካ ጠንካራ ሃገር ሆና ትቀጥላለች ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ዩናይትድ ስቴትስ ከበርካታ የአለም ሀገራት ወደ ግዛቷ በሚገቡ ምርቶች ላይ 10 በመቶ ታሪፍ መሰብሰብ የጀመረች ሲሆን በሚቀጥለው ሳምንትም ከፍተኛ ቀረጥ ተግባራዊ ታደርጋለች ተብሎ እየተጠበቀ ነዉ፡፡

አሜሪካ መሰረታዊ ታሪፍ ለመጀመሪያ ጊዜ ከጣለችባቸዉ ሀገራት መካከል አውስትራሊያ፣ ብሪታንያ፣ ኮሎምቢያ፣ አርጀንቲና፣ ግብፅ እና ሳዑዲ አረቢያ ይገኙበታል።

የዶናልድ ትራምፕ የወሰዱት እርምጃ ዓለም አቀፍ ገበያዎችን ወደ ውድቀት እያመራ መሆኑ እየተነገረ ባለበት በዚህ ወቅት የሃገሪቱ የአክሲዮን ገበያዎች የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ከተከሰተበት ጊዜ አንስቶ እጅግ የከፋ ነዉ የተባለለትን መቀዛቀዝ እያስተናገዱ መሆናቸዉ እየተነገረ ነዉ፡፡

አሜሪካ ታሪፍን እንደ መሳሪያ መጠቀሟን ተከትሎ ቻይና ገበያዉ መቀዛቀዙን ራሱ እየተናገረ ነዉ ስትል አስታዉቃለች፡፡ ለዚህም አሜሪካ ታሪፍን እንደ መሳሪያ መጠቀሟን ልታቆም ይገባል ስትል ቻይና አስጠንቅቃለች፡፡

የትራምፕ ተቃዋሚዎች በበኩላቸዉ ፕሬዝዳንቱና ቢሊዬነሩ ኤሎን መስክ በኢኮኖሚያዊ፤ በሰብአዊ መብቶችና በሌሎች ጉዳዮች ላይ እየወሰዱ ያሉትን እርምጃ ተከትሎ የተቃዉሞ ድምጽ ለማሰማት ማቀዳቸዉን አልጀዚራ ዘግቧል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review