ኢትዮጵያና እስራኤል ያላቸውን የንግድና ኢንቨስትመንት ግንኙነት አጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው አቶ አገኘሁ ተሻገር ገለጹ፡
የኢፌዲሪ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አገኘሁ ተሻገር ከ150ኛው የኢንተር ፓርላሜንታሪ ኅብረት/አይፒዩ/ መድረክ ጎን ለጎን በሁለትዮሽ ግንኙነት ዙሪያ የእስራኤል የፓርላማ ቡድን አባላትን አነጋግረዋል፡፡
አቶ አገኘሁ ኢትዮጵያና እስራኤል ዘመናትን የተሻገረ መልካም ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እንዳላቸው ጠቅሰው በንግድ፣ በኢንቨስትመንትና በቱሪዝም ያላቸውን ግንኙነት አጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው ተናግረዋል፡:
የኢትዮጵያ መንግሥት በሳይንስ፣ በቴክኖሎጂና በዘመናዊ ግብርና ዘርፎች ያለውን አሠራር አጠናክሮ መቀጠል እንደሚፈልግ ጠቅሰው በእነዚህ ዘርፎች ዙሪያ በትብብር መሥራት ሁለቱን አገራት ይበልጥ ውጤታማ እንደሚያደርጋቸው ያላቸውን እምነት አስረድተዋል፡፡ ኢትዮጵያ ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት እያሰመዝገበች የምትገኝ አገር መሆኗን በመግለፅ የእስራኤል ባለሃብቶች በልዩ ልዩ ዘርፎች ቢስማሩ ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ጥሪ አቅርበዋል።
በሌላ በኩል የእስራኤሉ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ( Speaker of the Knesset) አሚን ኦሃና እስራኤል ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ትሪካዊ ግንኝንት አጠናክራ እንደምትቀጥል አሁን ያለው አኮኖሚያዊና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ እንዲያድግ የሁለትዮሽ ግንኙነታችን ማጠናከር እንደሚገባና የምክር ቤቶችን የሁለትዮሽ ግንኙነት ትልቅ ትርጉም እንዳለው መናገራቸዉን ከፌዴሬሽን ምክር ቤት ያገኘነዉ መረጃ ያመላክታል፡፡
150ኛው የኢንተር ፓርላሜንታሪ ኅብረት/አይፒዩ/ ስብሰባ በኡዝቤኪስታን፣ ታሽከንት ከተማ እየተካሄደ መሆኑ ይታወቃል፡፡