ህዝቡ የሚያነሳቸው ጥያቄዎች በየደረጃዉ ምላሽ እንዲያገኙ ትኩረት ተሰጠቶ እንደሚሰራ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ቡዜና አልከድር ተናገሩ::
ህዝብን እና መንግስትን በማቀራረብ በአስፈፃሚው በኩል ለሕዝብ ተገቢውን ምላሽ እንዲሰጥ የሚያደርጉት የምክር ቤት አባላት በተመረጡበት አካባቢዎች ከህዝብ ጋር በመገናኘት የህዝቡን ጥያቄ እያደመጡ ይገኛል::
በየካ ክፍለ ከተማ የአዲስ አበባ ምክር ቤት ተመራጮችም ከክፍለ ከተማው ነዋሪ ጋር ምክክር እያደረጉ ነው::
በመድረኩ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ቡዜና አልከደርን ጨምሮ ክፍለ ከተማውን ወክለዉ ለአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የተመረጡ የምክር ቤት አባላት ተገኝተዋል ::
ወ/ሮ ቡዜና አልከድር በዚህ ወቅት እንዳሉት፣ ህዝቡ ከዚህ በፊት ሲያነሳቸዉ የነበሩ ጥያቄዎች ከአስፈፃሚ አካላት ጋር በመሆን ምላሽ እንዲያገኙ መደረጉን ተናግረዋል::
በቀጣይም ህዝቡ የሚያነሳቸው ጥያቄዎች በየደረጃዉ ምላሽ እንዲያገኙ ትኩረት ተሰጠቶ ይሰራልም ብለዋል::
በመድረኩም ባለፉት ጊዚያት የተከናወኑ የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችና የተከናወኑ የልማት ስራዎች ሪፖርት ቀርቧል::
በቴዎድሮስ ይሳ