በአቡዳቢ ዩኒቨርሲቲ የሚማሩ ተማሪዎች የኢትዮጵያን ባህል አስተዋወቁ

You are currently viewing በአቡዳቢ ዩኒቨርሲቲ የሚማሩ ተማሪዎች የኢትዮጵያን ባህል አስተዋወቁ

AMN – ሚያዝያ 01/2017

በአቡዳቢ ዩኒቨርሲቲ የሚማሩ ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲው በተካሄደው የባህል ሳምንት ላይ በመሳተፍ የአገራቸውን ባህል አስተዋውቀዋል::

በመርሃ ግብሩ ተማሪዎቹ በአገራችን በኢትዮጵያ የሚገኙ ባህላዊ፣ ሀይማኖታዊ እና ታሪካዊ ቅርሶችን፣ እንዲሁም የተለያዩ የሃገራችን ክፍሎችን የሚወክሉ የባህላዊ አመጋገብ፣ አለባበስ፣ ውዝዋዜ፣ ልዩ የሆነውን የኢትዮጵያውያን የቡና አፈላል ስነ ስርአት ለተለያዩ አገራት ዜጎች ማስተዋወቅ ችለዋል::

በአቡዳቢና አካባቢው የሚማሩ የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተማሪዎች በቅርቡ የተማሪዎች ማህበር በመመስረት ከአቡዳቢ የኢትዮጵያውያን ኮሚኒቲ ጽህፈት ቤት ስር እየተንቀሳቀሱ እንደሚገኙ በአቡዳቢ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመላክታል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review