ኮሚሽኑ በአማራ ክልል ከሚገኙ ተጽዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች ጋር እየተወያየ ነው

You are currently viewing ኮሚሽኑ በአማራ ክልል ከሚገኙ ተጽዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች ጋር እየተወያየ ነው

AMN – ሚያዝያ 01/ 2017

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በአማራ ክልል ከሚገኙ ተጽዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች እና ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት እያደረገ ይገኛል፡፡

በአማራ ክልል የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር ምዕራፍ እያካሄደ የሚገኘው የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከፓለቲካ ፓርቲ ተወካዮች ፣ ከምክር ቤት አባላትና ከክልሉ የስራ ሃላፊዎች እንዲሁም ከተለያዩተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦችና ከሲቪል ማህበራት ተወካዮች ጋር እየመከረ ነው።

የፓለቲካ ፓርቲ ተወካዮች ፣ የክልሉ የስራ ሃላፊዎች እንዲሁም የተለያዩ ተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦችና የሲቪልማህበራት ተወካዮች ከነገ ሀሙስ ሚያዝያ 02/2017 ጀምሮ አጀንዳዎቻቸውን መለየት ይጀምራሉ።

ተሳታፊዎች የሀገርን ህልውና የሚፈታተኑ ፣ ሀገራዊ አብሮነትን አደጋችየሚይደርጉ እንዲሁም በተለመደው የህግና የፖሊሲ ስርዓት ሊስተካከሉ የማይችሉ መሰረታዊ ጉዳዮች ላይ ትኩረት አድርገው መፍትሔ እንዲያፈላልጉ የአማራ ክልል የአጀንዳ ማሰባሰብ አስተባባሪ ኮሚሽነር መላኩ ወ/ማርያም ጥሪ አቅርበዋል።

በተሳታፊዎች የሚለዩ ጉዳዮች የክልሉ አጀንዳዎችሆነው ለብሔራዊ ምክክር ጉባኤ የሚቀርቡ ይሆናል።

በካሳሁን አንዱአለም

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review