ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን ለሚተኩ አምራች ኢንዱስትሪዎች ትኩረት ተሰጥቷል – አቶ መላኩ አለበል

You are currently viewing ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን ለሚተኩ አምራች ኢንዱስትሪዎች ትኩረት ተሰጥቷል – አቶ መላኩ አለበል

AMN – ሚያዝያ 1/2017 ዓ.ም

መንግስት ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን ለሚተኩ አምራች ኢንዱስትሪዎች እድገት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል ገለጹ።

አቶ መላኩ አለበል ሳቢያን ቤዝ ሜታል ኢንጂነሪንግ ተቋምን የስራ እንቅስቃሴ ጎብኝተዋል።

ሚኒስትሩ በጉብኝቱ ወቅት መንግስት ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ ምርት ለሚተኩ አምራች ኢንዱስትሪዎች መስፋፋት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

ዛሬ የተጎበኘው ሳቢያን ቤዝ ሜታል ኢንጂነሪንግ ከውጭ የሚገባውን የውሀ ቆጣሪ በሀገር ውስጥ ምርት በመተካት ረገድ ትልቅ አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል ብለዋል፡፡

መንግስት ይበለጠ ተኪ ምርትን የሚያመርቱ ፉብራካዎች እንዲስፋፉ እና ውጤታማ እንዲሆኑ ድጋፉና ክትትሉን አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ማስታወቃቸውም ኢዜአ ዘግቧል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review