3.4 ሚሊዮን ለሚሆኑ ዜጎች የሥራ ዕድል ተፈጥሯል

You are currently viewing 3.4 ሚሊዮን ለሚሆኑ ዜጎች የሥራ ዕድል ተፈጥሯል

AMN-ሚያዝያ 2/2017 ዓ.ም

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በዘጠኝ ወራት ውስጥ 3 ነጥብ 4 ሚሊዮን ለሚሆኑ ዜጎች የሥራ ዕድል መፍጠር መቻሉን ሚኒስትሯ ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል ገለፁ፡፡

ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል በግብርናው፣ በአገልግሎት እና በኢንዱስትሪው ዘርፎች ለበርካታ ዜጎች የሥራ ዕድል መፈጠር መቻሉን ዛሬ በተደረገው የሕዝብ ተወካዮች 23ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ አስረድተዋል፡፡

በሀገርው ስጥና ውጭ ሀገራት ዜጎችን በማሰልጠን እና በማብቃት በዘርፉ ተጠቃሚ እንዲሆኑ በተሰራው ስራ ውጤት ማምጣት መቻሉን ገልጸዋል፡፡

የሰው ሀብት ልማት፣ሥራ ሥምሪት እና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ነገሪ ሌንጮ (ዶ/ር) ተቋሙ የመንግስትን የአገልግሎት ማሻሻያ የሪፎርም ትግበራ፤ ለዜጎች የሥራ ዕድል ፈጣራ እንዲሁም ተቋሙ ቴክኖሎጂን በመጠቀም ለሰራው ስራ በጥንካሬ አንስተዋል፡፡

የሥራና አሰሪ አገናኝ ኤጀንሲዎች ጋር በተያያዘ እያጋጠመ ያለውን ችግር ለመቅረፍ ጥብቅ ክትትል እና ቁጥጥር ማድረግ እንደሚገባ የተ ነገሪ ሌንጮ (ዶ/ር) ማሳሰባቸዉን ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ማሕበራዊ ትስስር ገፅ ያገኘነው መረጃ ያሳያል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review