ከሸማችነት ወደ አምራችነት የሚደረገው ጉዞ የኢንዱስትሪውን ዘርፍ ከፍ ለማድረግ ይረዳል – አቶ ጃንጥራር አባይ

You are currently viewing ከሸማችነት ወደ አምራችነት የሚደረገው ጉዞ የኢንዱስትሪውን ዘርፍ ከፍ ለማድረግ ይረዳል – አቶ ጃንጥራር አባይ

AMN – ሚያዝያ 3/2017

ኢትዮጵያ-አዲስ አበባ ታምርት “ከሸማችነት ወደ አምራችነት” በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ አዘጋጅነት የፓናል ውይይት መርሃ ግብር እየተካሄደ ነው።

በአዲስ አለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል እየተካሄደ በሚገኘው የፓናል ውይይት፣ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ እና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጃንጥራር አባይ፣ ባስተላለፉት መልዕክት መድረኩ በዘርፉ የበለጠ ግንዛቤ ለመፍጠር እና የኢንዱስትሪውን ዘርፍ ከፍ ለማድረግ እንደሚረዳ ተናግረዋል፡፡

“ከሸማችነት ወደ አምራችነት” በሚል መሪ ሀሳብ እየተካሄደ ባለው በዚህ መድረክ፣ ዘርፉን የተመለከቱ ሀሳቦች እየቀረቡ ሲሆን የተለያዩ አምራቾች እና ባለድርሻ አካላትም እየተሳተፉ ይገኛሉ።

በሀብታሙ ሙለታ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review