በአማራ ክልል የምክክር መድረክ እየተሳተፉ የሚገኙ የአምስቱ ባለድርሻ አካላት ወኪሎች ከትላንት ጀምረው በባህር ዳር ከተማ አጀንዳዎቻቸውን በቡድን ውይይት እያደራጁ እንደሚገኝ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክር ኮሚሽን አስታወቀ።
ባለድርሻ አካላቱ ያደራጁትን አጀንዳ ለኮሚሽኑ የሚያቀርቡ 25 ተወካዮችን መርጠው አጀንዳዎቻቸውን በአደራ እንደሚያስረክቡ ኮሚሽኑ ገልጿል።
የሚመረጡት 25 ወኪሎች ነገ የክልሉን አጀንዳ በዋና መድረክ አቅርበው በማፅደቅ ለኮሚሽኑ እንደሚያስረክቡ ይጠበቃል።
በባለድርሻ አካላት ምክክር ምዕራፍ እየተሳተፉ የሚገኙት የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የመንግስት አስፈፃሚ አካላት፣ የህብረተሰብ ወኪሎች፣ የተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች እንዲሁም የልዩ ልዩ ተቋማትና ማህበራት ወኪሎች ናቸው።
የአማራ ክልል የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር መድረክ ነገ እንደሚጠናቀቅ የኮሚሽኑ መረጃ ያመለክታል።