በሀገር ጉዳይ እኩል የመወሰንና የፍትሃዊ ተጠቃሚነት ጉዳይ በለውጡ መንግስት ምላሽ አግኝቷል

You are currently viewing በሀገር ጉዳይ እኩል የመወሰንና የፍትሃዊ ተጠቃሚነት ጉዳይ በለውጡ መንግስት ምላሽ አግኝቷል

AMN – ሚያዝያ 3/2017 ዓ.ም

በሀገር ጉዳይ እኩል የመወሰን፣ በጋራ የመልማት እና የፍትሃዊ ተጠቃሚነት ጉዳይ በለውጡ መንግስት ምላሽ ያገኘ መሆኑን በብልጽግና ፓርቲ የጋምቤላ፣ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ እና የአፋር ክልል ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቶች ኃላፊዎች ገለጹ።

በብልጽግና ፓርቲ የጋምቤላ፣ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ እና የአፋር ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቶች ሃላፊዎች፤ ለውጡን ተከትሎ በፓለቲካው ከዳር ተመልካችነት በመውጣት በሀገር ጉዳይ በጋራ በመወሰን ላይ እንገኛለን ብለዋል።

የለውጡ መንግስት አካታችና ህብረ ብሄራዊ ሀገራዊ ፓርቲ በመመስረት ኢትዮጵያን በጋራ መምራት እንደሚገባ በተግባር አሳይቷል ሲሉም ገልጸዋል።

በብልጽግና ፓርቲ የጋምቤላ ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አሸኔ አስቲን፣ የጋምቤላ ክልል ለረጅም ዓመታት በሀገር ጉዳይ እኩል የመወሰንና የልማት ነፃነት ተነፍጎት መቆየቱን አስታውሰው፣ ለውጡን ተከትሎ የዚሁ አግላይ ፖለቲካ ሰላባ የነበሩ ሁሉ ሙሉ የመወሰን ስልጣን እንዲኖራቸው መደረጉን አንስተዋል።

በብልጽግና ፓርቲ የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃለፊ አቶ ኢሳቅ አብዱልቃደር፣ አጋር መባል ቀርቶ በለውጡ በጋራ ሀገር የመምራት እኩል ተሳትፎና ልማት እድል አግኝተናል ብለዋል።

በብልጽግና ፓርቲ የአፋር ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ መሐመድ ሁሴን በበኩላቸው፣ የአፋር ክልል እምቅ ሀብት እያለው መጠቀም ሳይችል መቆየቱን አንስተው፣ በለውጡ ሃብቱን በአግባቡ ማልማትና መጠቀም እንደቻለ መግለፃቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review