የሆሳዕና በዓል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሀይማኖት ተከታዮች ዘንድ በድምቀት እየተከበረ ነው

You are currently viewing የሆሳዕና በዓል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሀይማኖት ተከታዮች ዘንድ በድምቀት እየተከበረ ነው

AMN- ሚያዝያ 5/2017 ዓ.ም

የሆሳዕና በዓል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሀይማኖት ተከታዮች ዘንድ በድምቀት በመከበር ላይ ነው።

የሆሳዕና በዓል በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያሪክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት በተገኙበት እየተከበረ ነው።

በዓሉ የእምነቱ ተከታዮች በተገኙበት የእለቱን የቅዳሴ መርሐ-ግብር በመከታተል እና በሌሎች ሃይማኖታዊ ስነ-ስርዓቶች እየተከበረ ይገኛል።

ዐቢይ ፆም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ካሉ አፅዋማት መካከል አንዱ ነው፡፡

የእምነቱ ተከታዮች ከየካቲት 17 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ በፆም እና በፀሎት ያሳለፉ ሲሆን ዛሬ የፆሙን የመጨረሻ ሳምንት የሆነውን የሆሳዕና በዓል በማክበር ላይ ይገኛሉ።

በጺዮን ማሞ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review