የኢትዮጵያ አየር መንገድ በሚሰጣቸው ዘመናዊ አገልግሎቶች ሁለት ሽልማቶችን ተቀዳጀ

You are currently viewing የኢትዮጵያ አየር መንገድ በሚሰጣቸው ዘመናዊ አገልግሎቶች ሁለት ሽልማቶችን ተቀዳጀ

AMN – ሚያዝያ 06/2017

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በሚሰጣቸው ዘመናዊ አገልግሎቶች በጀርመን ሀምቡርግ በተካሄዱ ሁለት መርሃግብሮች ሁለት ሽልማቶችን ተቀዳጅቷል፡፡

አየር መንገዱ “በአፍሪካ ምርጥ የበረራ ላይ ምግብ አቅርቦት አየር መንገድ” ሽልማት እና በአፍሪካ በቀዳሚነት በተረከባቸው ኤርባስ A350-1000 አውሮፕላኖቹ በሚሰጣቸው ዘመናዊ አገልግሎቶች “Cabin Concept of the Year 2025” ሽልማት መቀዳጀቱን ከአየር መንገዱ ያገኘነዉ መረጃ ያመላክታል፡፡

ሽልማቶቹ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለሚሰጣቸው አገልግሎቶች ዓለም አቀፍ እውቅና ያጎናፀፉና በዓለም ደረጃ ያለውን ተወዳዳሪነት የሚያጠናክሩ መሆናቸዉ ተገልጿል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review