በትንሳዔ በዓል የምርት አቅርቦት እጥረት እንዳያጋጥም በቅንጅት እየተሰራ ነው – አቶ ጃንጥራር አባይ

You are currently viewing በትንሳዔ በዓል የምርት አቅርቦት እጥረት እንዳያጋጥም በቅንጅት እየተሰራ ነው – አቶ ጃንጥራር አባይ

AMN – ሚያዝያ 06/2017

በትንሳዔ በዓል የምርት አቅርቦት እጥረት እንዳያጋጥም በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ እና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጃንጥራር አባይ ገለጹ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኑሮ ውድነትና ህገ ወጥነት የመከላከል ግብረ ኃይል መጪው የትንሳኤ በዓልን አስመልክቶ ከምርት አቅርቦት ጋር ተያይዞ የተከናወኑ እና እየተከናወኑ የሚገኙ ስራዎችን ገምግሟል።

ገብረሃይሉ በግምገማው ከትንሳኤ በዓል ጋር ተያይዞ በርከት ያሉ ስራዎች መከናወናቸውን ተመልክቷል።

የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ እና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ እንዲሁም የግብረሃይሉ ሰብሳቢ አቶ ጃንጥራር አባይ ፤ በትንሳዔ በዓል የምርት አቅርቦት እጥረት እንዳይከሰት በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

በመሠረታዊ ምርቶች ላይ ምንም አይነት እጥረት እንደሌለ የገለጹት አቶ ጃንጥራር፣ ለዚህም ይረዳ ዘንድ በሁሉም የገበያ አማራጮች ምርቶች እየቀረቡ ነው ብለዋል።

በሀብታሙ ሙለታ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review