“ስፖርት ለልማትና ለሠላም” በሚል መሪ ሐሳብ በደምቢዶሎ ከተማ የማህበረሰብ አቀፍ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ እየተካሄደ ነው::
5ኛውን ሀገር አቀፍ ስፖርት ለልማትና ለሰላም ቀንን ምክንያት በማድረግ በደምቢዶሎ ከተማ የማህበረሰብ አቀፍ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በቄለም ወለጋ ዞን ደምቢዶሎ ከተማ እየተካሄደ ነው።
በአካል ብቃት እንቅስቃሴው ላይ የባህል እና ስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ መክዩ መሐመድ፣ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ፕሬዚዳንት ኢሳያስ ጅራ፣ የክልል የስራ ሃላፊዎች፣ የዞኑ አመራሮችን ጨምሮ በርካታ የደምቢዶሎ ከተማ ነዋሪዎች እየተሳተፉ ይገኛሉ።
ስፖርት ለልማትና ለሰላም ቀን በሀገር አቀፍ ደረጃ ለ5ኛ እና በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ12ኛ ጊዜ እየተከበረ እንደሚገኝ ኢዜአ ዘግቧል፡፡