ኢትዮጵያ የህዝብ ማመላለሻ ሞዳል ፈረቃን በማስተዋወቅ ላደረገችው ልዩ ጥረት ዛሬ በኢስዋቲኒ የእውቅና ሽልማት ማግኘቷን የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር አስታውቋል።
ሽልማቱን የሰጡት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሀፊ የመንገድ ደህንነት ልዩ መልዕክተኛ ሚስተር ዣን ቶድት ከኢስዋቲኒ ኪንግደም ጠቅላይ ሚኒስትር ጋር በመሆን ነው ተብሏል።
ይህ ሽልማት ኢትዮጵያ ዘላቂ፣ ደህንነቱ የተጠበቀ እና ቀልጣፋ የህዝብ ማመላለሻ ስርዓቶችን ለማራመድ ያላትን ቁርጠኝነት እንደሚያሳይ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር መረጃ ያሳያል።
የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዴኤታ በርኦ ሀሰን ሽልማቱን የተቀበሉ ሲሆን ለቀጣይ ጥረት ትልቅ ማበረታቻ እንደሚሆን ገልጸዋል።