የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2017 የትንሳኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ ለ200ሺ ዜጎች ማዕድ አጋርቷል፡፡
በከንቲባ ጽህፈት ቤት ለ5ሺ አቅመ ደካሞች ማዕድ ያጋሩት የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ ከሀገራዊ ለውጡ በኋላ የሰው ተኮር ፕሮግራሞችን የፖለቲካ ፕሮግራም አካል በማድረግ ማህበራዊ ስብራቶችን እየጠገንበት እንገኛለን ብለዋል።
በዓላትና የኑሮ ጫና ያስከተሉ ወቅቶችን ታሳቢ በማድረግ ለአቅመ ደካሞች ማዕድ ስናጋራ ቆይተናል ያሉት ከንቲባ አዳነች፣ በ2017 ዓ.ም ብቻ መርሐ-ግብሩ ለስምንተኛ ዙር መካሄዱን አስታውቀዋል።
ከተማ አስተዳደሩ ቀደም ብሎ የኢድ አልፈጥርን በዓል ምክንያት በማድረግ ለ100 ሺ ነዋሪዎች ማዕድ መጋራቱን የገለጹት ከንቲባ አዳነች፣ የትንሳኤ በዓልን በማስመልከትም በሁሉም ክፍለ ከተሞች እና ወረዳዎች ለ200 ሺህ ነዋሪዎች ማዕድ መጋራቱን አስታውቀዋል።
መስጠት አያጎልም ያሉት ከንቲባ አዳነች ለማዕድ ማጋራት መርሐ-ግብሩ አስተዋጽኦ ያደረጉ አካላትንም አመስግነዋል።
በሰብስቤ ባዩ