የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የትንሳኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ ለ990 የሕግ ታራሚዎች ይቅርታ አድርጓል።
ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ መጪውን የትንሳኤ በዓል ምክንያት በማድረግ፤ የክልሉ መንግስት የይቅርታ አዋጁን መስፈርት ላሟሉ 990 የሕግ ታራሚዎች ይቅርታ ማድረጉን አስታውቀዋል፡፡
ይቅርታው ከተደረገላቸው 990 የሕግ ታራሚዎች መካከል፡- 985ቱ በሙሉ ይቅርታ ከእስር የሚፈቱ ሲሆን፤ ቀሪ 5 ታራሚዎች የእስራት ጊዜያቸው የተቀነሰላቸው መሆኑን ገልፀዋል።
የይቅርታ ተጠቃሚ ከሆኑት የሕግ ታራሚዎች መካከል 73ቱ ሴቶች ሲሆኑ፤ 917ቱ ደግሞ ወንዶች መሆናቸውን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጽህፈት ቤት መረጃ ያመለክታል።