በ9 ወራት ውስጥ 26 ቶን ወርቅ ለብሔራዊ ባንክ ቀርቦ ከ2.1 ቢሊዮን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሬ ማግኘት መቻሉ ተገለፀ፡፡
የማዕድን ሚኒስቴር እና የተጠሪ ተቋማት አመራሮችና እና ሠራተኞች ባለፉት 9 ወራት በተመዘገቡ ሃገራዊ አፈጻጸሞች ዙሪያ ውይይት አካሂደዋል፡፡
በውይይቱ የጠቅላዩ ሚኒስትሩ የወጣቶችና ስፖርት አማካሪ አቶ ቀጃላ መርዳሳ የተገኙ ሲሆን ማዕድን ከሌሎች ዘርፎች የላቀ ውጤት የተመዘገበበት መሆኑን ተናግረው በቀጣይ በስኬቱ ሳይዘናጉ ውጤቱን ማስቀጠል ይገባል ብለዋል፡፡
የውይይቱ ተሳታፊዎችም በ9 ወራት የተመዘገበው የሁሉም ዘርፎች ሃገራዊ አፈጻጸም መቅረቡ ለቀጣይ ሃገራዊ ተልዕኮ የሚያነሳሳ መሆኑን መግለጻቸዉን ከማዕድን ሚኒስቴር ያገኘነዉ መረጃ ያመላክታል፡፡