አፈ ጉበኤ ወ/ሮ ቡዜና አልከድር እና የምክር ቤቱ ከፍተኛ አመራሮች የከተማዋን የበአል ግብይት እንቀስቃሴ ጎበኙ

You are currently viewing አፈ ጉበኤ ወ/ሮ ቡዜና አልከድር እና የምክር ቤቱ ከፍተኛ አመራሮች የከተማዋን የበአል ግብይት እንቀስቃሴ ጎበኙ

AMN – ሚያዝያ 08/2017

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ቡዜና አልከድር ፣ ወ/ሪት ፋኢዛ መሀመድ እና የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ማሾ ኦላና በተለያዩ ክፍለ ከተሞች በመገኘት የበአል ግብይት እንቀስቃሴን ጎብኝተዋል፡፡

አመራሮቹ በየካ ፣ ቦሌ ፣ አቃቂ እና ንፋስ ስልክ ክፍለ ከተሞች በመገኘት ምልከታ ያደረጉ ሲሆን በዓሉን ታሳቢ ያደረጉ ባዛሮች በሁሉም ወረዳዎች መከፈታቸውና ህዝቡ የበዓል ግብዓቶችን አጥጋቢ በሆነ ሁኔታ ማግኘት እንዲችልና እንዲገበያይ መደረጉን አድንቀዋል።

ይሁን እንጂ በአንዳንድ ገበያ ቦታዎች እና የሸማች ሱቆች ነጋዴው በለጠፈው ዋጋ መሰረት ያለመሸጥ፣ አንዳንድ ለገበያ የቀረቡ ግብዓቶች የጥራት ችግር ያለባቸው መሆኑ እና ግብዓቶች በበቂ ሁኔታ ያለመቅረብ ችግር በስፋት ተስተውሏል።

በበዓሉ ሰበብ አላስፈላጊ የዋጋ ጭማሪ እንዳይደረግ፣ ጥራት እንዳይጓደልና እጥረት እንዳያጋጥም በሚመለከታቸው የንግድና ሌሎች መንግስታዊ ተቋማት እየተደረገ ያለው ክትትልና ቁጥጥር ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ሲሉ ማሳሰባቸውን ከከተማዉ ምክር ቤት ያገኘነዉ መረጃ ያመላክታል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review