ኢ-ተገማች በሆነው የዓለም ሁኔታ የሚፈጠሩ ዕድሎችን በአግባቡ ለመጠቀም ይበልጥ መስራት ይገባል-ዶ/ር አብርሃም በላይ

You are currently viewing ኢ-ተገማች በሆነው የዓለም ሁኔታ የሚፈጠሩ ዕድሎችን በአግባቡ ለመጠቀም ይበልጥ መስራት ይገባል-ዶ/ር አብርሃም በላይ

ኢ-ተገማች በሆነው የዓለም ሁኔታ የሚፈጠሩ ዕድሎችን በአግባቡ ለመጠቀም ይበልጥ መስራት ይገባል-ዶ/ር አብርሃም በላይ

AMN-ሚያዝያ 9/2017 ዓ.ም

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋማት ሰራተኞች እና አመራሮች በ2017 ዓ.ም የዘጠኝ ወራት አገራዊ እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ላይ ውይይት አድርገዋል።

በመድረኩ የአፈፃፀም ሪፓርቱን ያቀረቡት የኢትዮጵያ ዲያስፖራ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ፍፁም አረጋ፣ ባለፉት ዘጠኝ ወራት የነበረው የማክሮ ኢኮኖሚ አፈፃፀም ምርታማነትን እና ተወዳዳሪነትን ማሳደግ ያስቻለ ነው ብለዋል።

በ2017 ዓ.ም ዘጠኝ ወራት ኢኮኖሚው በ8.4 በመቶ ማደጉ የተገለፀ ሲሆን 5.2 ቢሊየን ዶላር ከወጪ ንግድ መገኘቱ ተመላክቷል።

በዘጠኝ ወሩ ውጭ ከሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በሬሚታንስ ከ3.6 ቢሊየን ዶላር በላይ ገንዘብ ወደ ሃገር ውስጥ የተላከ ሲሆን ከአምና ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፃር 12 በመቶ እድገት እንዳለው ተጠቅሷል።

መድረኩን በአወያይነት የመሩት የመስኖ እና ቆላማ አካባቢ ሚኒስትር ዶ/ር አብርሃም በላይ፤ ባለፉት ሰባት አመታት የተተገበሩ ሁለንተናዊ የሪፎርም ስራዎች የኢትዮጵያን የእድገት ማነቆዎች ለመፍታት ያስቻሉ እና ሉዐላዊነትን ለማረጋገጥ ያስቻሉ እንደሆነ ተናግረዋል ።

በመጪው ጊዜ የሚፈጠሩ እድል እና ስጋቶችን በጥልቀት በመመዘን ጥቅምን ለማሳደግ መሰራት እንዳለበትም መናገራቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያሳያል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review