ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽንን የስራ እንቅስቃሴ ጎበኙ

You are currently viewing ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽንን የስራ እንቅስቃሴ ጎበኙ

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽንን የስራ እንቅስቃሴ ጎበኙ

AMN-ሚያዚያ 09/2017 ዓ.ም

ዛሬ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ተገኝተው የኮሚሽኑን የስራ እንቅስቃሴ መመልከታቸውን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉብኝታቸውን አስመልክተው በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባጋሩት መልዕክት፣ ኮሚሽኑ ባለፉት የለውጥ ዓመታት የኢትዮጵያን የኢንቨስትመንት ምህዳር በእጅጉ ያሻሻሉ የሪፎርም ተግባራትን ማከናወኑን መመልከታቸውን ገልጸዋል።

ተቋሙ ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ እና ዘመናዊ የዲጂታል አሰራሮችን የተከተለ የደንበኞች አገልግሎት አሰራርን ተግባራዊ አድርጎ እየሰራ ይገኛልም ብለዋል፡፡

የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው ለዘርፉ ትልቅ ዕድል የከፈተ መሆኑን የገለጹ ሲሆን በበጀት ዓመቱ ዘጠኝ ወራት የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንትን በመሳብ ረገድ የተገኘው ስኬትም ይህንኑ የሚያሳይ መሆኑን ጠቁመዋል።

በቀጣይ ኮሚሽኑ የጀመረውን አበረታች እና ከኢኮኖሚ ዕቅዶች ጋር የተጣጣመ ዒላማ ተኮር የኢንቨስትመንት አማራጮችን በማስተዋወቅ የኢንቨስትመንት ፍሰትን ማሳደግ ላይ በትኩረት እንዲሰራ አቅጣጫ ማስቀመጣቸውንም አብራርተዋል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review