የ2017 ዓ.ም የትንሳኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ቡዜና አልከድር በምክር ቤቱ ጽ/ቤት በስራ ላይ ላሉ የፀጥታ አካላት ማዕድ አጋርተዋል።
በአዲስ አበባ ከተማ የተመዘገበው ሰላም የፀጥታ አካላት ጠንካራ የህዝብ ውግንና ፣ የፖሊሳዊ ስነ ምግባር እና የስራ ትጋት ውጤት መሆኑን አፈ ጉባኤዋ ገልጸዋል፡፡
በቀጣይም ይህን ሰላም ጠብቆ በማዝለቅ ረገድም በጽናት እንዲቆሙ ጥሪ ማቅረባቸውን ከምክር ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡