የፌደራል ፖሊስ ለፋሲካ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፈ

You are currently viewing የፌደራል ፖሊስ ለፋሲካ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፈ

AMN – ሚያዝያ 11/2017

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለፋሲካ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ሲል የመልካም ምኞት መልዕክቱን አስተላልፏል።

የፌደራል ፖሊስ በመልዕክቱ፣ የዕምነቱ ተከታዮች በዓሉን ያለምንም የፀጥታ ሥጋት በሰላምና በደስታ እንዲያከብሩ ፌደራል ፖሊስ ከሌሎች የፀጥታ እና ደኅንነት አካላት ጋር በመቀናጀት አዲስ አበባ ከተማን ጨምሮ በመላው የሀገራችን አካባቢዎች በሰላማዊ ሁኔታ እንዲከበር በቂ ዝግጅት አድርጎ ወደ ሥራ በመግባት ፖሊሳዊ ተልዕኮውን በብቃት እና በቁርጠኝነት እየተወጣ እንደሚገኝ ገልጿል።

መላው የሀገራችን ሕዝብ ለበዓሉ መከበር እንቅፋት ሊሆኑ የሚችሉ ነገሮችን ለማስወገድ በሚካሄደው የፀጥታ ማስከበር ሥራ ላይ በባለቤትነት በመሳተፍ እያደረገ ያለውን እንቅስቃሴ የበለጠ አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ነው ያመለከተው፡፡

ህብረተሰቡ የፀጥታ ስጋት ሊሆኑ የሚችሉ አጠራጣሪ ነገሮችን ሲመለከት በዜጎች ተሳትፎ መተግበሪያ (EFP App) እና በ991 ነፃ የስልክ መስመር ጥቆማ በመስጠት የዜግነት ድርሻውን እንዲወጣ የፌደራል ፖሊስ ጥሪውን አቅርቧል።

የሕዝብን ጥቅም አስቀድማችሁ ከቤተሰቦቻችሁ ርቃችሁ በዓሉን ግዳጅ ላይ ሆናችሁ የምታሳልፉ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ሠራዊት፣ የከተማና የክልል ፖሊስ አመራርና አባላት፣ እንዲሁም ሌሎች የፀጥታና ደህንነት ኃይሎች የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ እንኳን ለፋሲካ በዓል በሰላም አደረሳችሁ በማለት በዓሉ የሰላም፣ የጤና፣ የፍቅርና የአብሮነት እንዲሆን መልካም ምኞቱን ገልጿል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review