በከተማዋ የሚገኙ ባለሀብቶችን በማስተባበር በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ዜጎችን ህይወት የመለወጡ ተግባር ተጠናክሮ ይቀጥላል- አቶ ሞገስ ባልቻ

You are currently viewing በከተማዋ የሚገኙ ባለሀብቶችን በማስተባበር በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ዜጎችን ህይወት የመለወጡ ተግባር ተጠናክሮ ይቀጥላል- አቶ ሞገስ ባልቻ

AMN- ሚያዝያ 11/2017 ዓ.ም

በከተማዋ የሚገኙ ባለሀብቶችን በማስተባበር በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ዜጎችን ህይወት የመለወጡ ተግባር ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉ በብልጽግና ፓርቲ አዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ ተናገሩ፡፡

በልደታ ክፍለ ከተማ የትንሳኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ 4 ቤቶችን በበጎፍቃድ ባለሀብት በማስገንባት በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ ዜጎች ተላልፈዋል፡፡

በብልጽግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ፤ ከተማ አስተዳደሩ በጉብዝናቸው ወራት ሀገርን ያገለገሉና ባለውለታዎችን አቅማቸው ሲዝል አይዟችሁ፤ አለሁላችሁ እያለ ይገኛል ብለዋል፡፡ በለውጡ ዓመታት በጎፍቃደኞችን በማስተባበርም በርካታ ቤቶች ተገንብተው ለእነዚህ ዜጎች እንዲተላለፉ ስለመደረጉም ነው የገለጹት፡፡

ከተባበርን ሀገርን ከድህነት ማውጣት እንደሚቻል ባለፉት ዓመታት የተሰሩት ሰው ተኮር ስራዎች ማሳያ ናቸው ያሉት አቶ ሞገስ ይህንን ተግባር አጠናክሮ ማስቀጠል ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

በክፍለ ከተማው ባለፉት 9ወራት በበጎ ፍቃደኞች 249 ቤቶች ታድሰው ለተጠቃሚዎች እንዲተላለፉ ተደርገዋል ያሉት የልደታ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ ወ/ሮ አበባ እሸቴ የትንሳኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ በሁሉም ወረዳዎች ቤቶች እየታደሱ ለነዋሪዎች እየተሰጡ ነው ብለዋል፡፡

ለረዥም ዓመታት በከፋ ችግር ውስጥ እንደነበሩ የገለጹት ቤታቸው ታደሶ የተሰጣቸው ነዋሪዎች በበኩላቸው ቤታቸው መታደሱ እንዳስደሰታቸው ገልጸው ምስጋና አቅርበዋል፡፡

በክፍለ ከተማው ቤት ከማደስ ባለፈ ለበዓል መዋያ የተለያዩ ስጦታዎች ተበርክቶላቸዋል፡፡

በሄለን ጀንበሬ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review