የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በ2017 በጀት ዓመት ዘጠኝ ወራት በርካታ ሕገ- ወጥ የጦር መሣሪያዎችን ከ146 ተጠርጣሪዎች ጋር በቁጥጥር ሥር ማዋሉን ገልጿል።
የተለያዩ ሕገ-ወጥ የጦር መሣሪያ ዝውውርን ለመከላከል በተደረገው ኦፕሬሽን 121 የጦር መሣሪያዎችን ከመኖሪያ ቤቶች፣ 8 ሺህ 989 ከፀረ-ሰላም ኃይሎች፣ 36 የጦር መሣሪያዎችን ደግሞ በኬላዎች ላይ መያዙ ታውቋል።
6 ሺህ 351 የተለያዩ የጦር መሣሪያ ጥይቶች ከመኖሪያ ቤቶች፣ 8 ሺህ 989 ከፀረ-ሰላም ኃይሎች፣ 51 ሺህ 846 በኬላዎች የያዘ ሲሆን 236 የተለያዩ የጦር መሣሪያ ካዝናዎች በመኖሪያ ቤቶች፣ 148 በኬላዎች ላይ መያዛቸው ተገልጿል።
በተመሳሳይ አንድ ብሬን ከፀረ-ሰላም ኃይሎች፣ ሁለት ብሬን በኬላዎች የተያዘ ሲሆን 31 የተለያዩ ቦምቦች ከመኖሪያ ቤቶች፣ 25 ቦምቦችን ከፀረ-ሰላም ኃይሎች፣ 122 ቦምቦችን በኬላዎች መያዙ በሪፖርቱ ተመላክቷል።
በተጨማሪ 32 የተለያዩ ሕገ-ወጥ ሽጉጦች ከመኖሪያ ቤቶች፣128 ሽጉጦች ከፀረ-ሰላም ኃይሎች፣ 102 በኬላዎች መያዝ የተቻለ ሲሆን እንድ ስናይፐር ከመኖሪያ ቤቶች፣ አንድ ስናይፐር ደግሞ ከፀረ-ሰላም ኃይሎች በኤግዚቢትነት ይዞ ከ146 ተጠርጣሪዎች ጋር በቁጥጥር ሥር ማዋሉን ከኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ያገኘነዉ መረጃ ያሳያል፡፡