የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን መንበር እረኛ ብጹዕ ወቅዱስ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ከዚህ ዓላም ድካም በማረፋቸውን የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ገልጿል።
ጉባኤው ባወጣው የሀዘን መግለጫ፣ ብጹዕ ወቅዱስ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በ88 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም ድካም ያረፉ ቢሆንም በሕይወት በነበሩበት ጊዜ ለመላው የካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ለሰጡት መንፈሳዊ አገልግሎት እና አመራር እንዲሁም ለዓለም ሰላም ላበረከቱት የላቀ አበርክቶ ዘወትር ሲታወሱ ይኖራሉ ብሏል፡፡
በብጹዕ ወቅዱስ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ሕልፈተ ሕይወት ምክንያት ከፍተኛ ሀዘን ውስጥ ለሚገኙት የካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች እና ምዕምናን በሙሉ መፅናናትን ተመኝቷል።