የአምስት ሚሊዮን ኮደርስ ስልጠና በዲጂታል ቴክኖሎጂ እውቀት የጎለበቱ ሙያተኞችን ለማፍራት ያስችላል- ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ

You are currently viewing የአምስት ሚሊዮን ኮደርስ ስልጠና በዲጂታል ቴክኖሎጂ እውቀት የጎለበቱ ሙያተኞችን ለማፍራት ያስችላል- ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ

AMN – ሚያዝያ 14/2017 ዓ.ም

የአምስት ሚሊዮን ኮደርስ ስልጠና በዲጂታል ቴክኖሎጂ እውቀት የጎለበቱ ሙያተኞችን ለማፍራት እንደሚያስችል በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ ተናገሩ::

የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ለ2ኛ ጊዜ የአምስት ሚሊዮን ኮደርስ ስልጠና የወሰዱ 127 ሙያተኞቹን አስመርቋል::

በመርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ፣ የአምስት ሚሊዮን ኮደርስ ስልጠና በዲጂታል ቴክኖሎጂ እውቀት የጎለበቱ ሙያተኞችን ለማፍራት እንደሚያስችል ገልጸዋል::

አዲስ አበባ ከተማ በእድገት ጎዳና ላይ እንደምትገኝ የገለፁት ኢንጂነር ወንድሙ፣ ይህንን የሚመጥን የሰዉ ሃይል ለመገንባት እየተሰራ ነዉ ብለዋል::

በስልጠናው ከወረዳ እስከ ከማዕከል የሚገኙ የኤጄንሲው ባለሙያዎች መሳተፋቸውም ተመላክቷል።

በቴዎድሮስ ይሳ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review