ቦይንግ የአፍሪካ ቢሮውን በአዲስ አበባ ከፈተ

You are currently viewing ቦይንግ የአፍሪካ ቢሮውን በአዲስ አበባ ከፈተ

AMN- ሚያዝያ 14/2017 ዓ.ም

የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር) ቦይንግ የአፍሪካ ቢሮውን በአዲስ አበባ መክፈቱ ዓለማቀፋዊ ራዕያችንን ለማሳካት ወሳኝ እርምጃ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ሚኒስትሩ የቦይንግ ኩባንያ የአዲስ አበባ ቢሮውን በከፈተበት ስነስርዓት ላይ ተገኝተው የቢሮው መከፈት በዓለም አቀፉ አቪዬሽን የኢትዮጵያን እድገት ማሳያ ከመሆን ባሻገር፣ የተሳሰረችና የበለፀገች አፍሪካን እውን የማድረግ ዓለም አቀፋዊ ራዕያችንን ለማሳካት የሚያግዝ እርምጃ ነው ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያ እያደገ የመጣ የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ አቅም መፍጠሯን የጠቆሙት ሚኒስትሩ፣ በብሔራዊ ትራንስፖርት ካውንስል የሚመራ የዘርፉን መሠረተ-ልማት ለማዘመን፣ የትራንስፖርት ንግድ ወጪን ለመቀነስ እና አፍሪካን ለማስተሳሰር የሚያስችል የአስርት አመታት ፍኖተ ካርታ አዘጋጅተን እየሰራን ነው ብለዋል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review