የመጀመሪያው ምዕራፍ የአዲስ አበባ ኮሪደር ልማት መጠናቀቅን ተከትሎ በአሁኑ ወቅት በመልሶ ግንባታ ውስጥ ካሉ ስምንት ዐበይት ኮረደሮች አንዱ የካዛንቺስ አካባቢ ነው።

You are currently viewing የመጀመሪያው ምዕራፍ የአዲስ አበባ ኮሪደር ልማት መጠናቀቅን ተከትሎ በአሁኑ ወቅት በመልሶ ግንባታ ውስጥ ካሉ ስምንት ዐበይት ኮረደሮች አንዱ የካዛንቺስ አካባቢ ነው።

በአንድ ወቅት ከተዘነጉ የማዕከላዊ አዲስ አበባ ስፍራዎች አንዱ የሆነው ካዛንቺስ አካታች እና ተደራሽነቱ የተስፋፋ ሕዝባዊ ስፍራ እንዲሆን በአዲስ ምናብ ተቃኝቷል። መልሶ ማልማቱ አስፋልት መንገዶችን፣ የእግረኞች መንገዶችን፣ የብስክሌት መንገዶችን፣ የሕፃናት መጫወቻዎችን፣ የስፖርት መሠረተ ልማቶችን፣ የሕዝብ ፕላዛዎችን፣ አረንጓዴ ፓርኮችን፣ የሕዝብ መጸዳጃዎችን፣ ሱቆችን እና የመኪና ማቆሚያዎችን ያካተተ ነው።

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር እንደገለፁት የካዛንቺስ መልሶማልማት በአገልግሎትም በእኩል ተጠቃሚነትም ኅብረተሰብን እንዲያገለግል የተቀረፀ ነው። “በአስደናቂ አጭር ጊዜ የተጠናቀቀው የካዛንቺስ ለውጥ ለዘመነ ከተማ ልማት ሥራችን ለአረንጓዴ፣ ንፁህ እና ዘመናዊ የከተማ ማዕከላት መሠረት የሚጥል ነው።” ብለዋል።

ቀጥሎ የተያያዘው ቪዲዮ ጠቅላይ ሚኒስትር፣ ቀዳማዊት እመቤት እና ሌሎች ከፍተኛ የመንግሥት ኃላፊዎች በተገኙበት በሚያዚያ 15 ቀን 2017 የተመረቀውን የካዛንቺስ ኮሪደር ልማት ይፋዊ የምረቃ ሥነ ሥርዓት ያሳያል – የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review