ካዛንቺስ – እንደገና በልዩ ሁኔታ ስለተወለድሽ እንኳን ደስ ያለሽ – ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

You are currently viewing ካዛንቺስ – እንደገና በልዩ ሁኔታ ስለተወለድሽ እንኳን ደስ ያለሽ – ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

AMN – ሚያዝያ 15/2017

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸዉ ባሰፈሩት መልእክት ካዛንቺስ የድካማችን ትእምርት፣ የስንፍናችን ሰንደቅ ነበረች። የቤተ መንግሥት ጎረቤት መሆንዋ ዓይነ ጥላ የሆነባት።

ዛሬ ካዛንቺስ የኢትዮጵያ ትንሣኤ ምልክት ናት። ከተማ እንዴት መልሶ እንደሚገነባ ህያው ትምህርት ቤት ናት። ንግድ፣ አገልግሎት፣ መዝናኛ፣ መሠረተ ልማት፣ እንዴት በብልጽግና ሐሳብ እንደሚገነቡ አጉልታ ታሳያለች፤ ጮኻ ትናገራለች። ለሕጻናት፣ ካዛንቺስ ለወጣቶች፣ ለጎልማሶች፣ ለአረጋውያን፣ የሚሆን ከተማ ምን እንደሚመስል በኤግዚቢሽንነት ታስረዳለች። የሴቶችን ክብር ከፍ ታደርጋለች።

ካዛንቺስ – እንደገና በልዩ ሁኔታ ስለተወለድሽ እንኳን ደስ ያለሽ። አንቺን የፈጠረ ሐሳብ፣ የገነቡ እጆች – አስደናቂ ናቸው ብለዋል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review