የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬሕይወት ታምሩ ከቪዛ ኢንክ የደቡብ እና ምስራቅ አፍሪካ ሪጅኖች ምክትል ፕሬዝዳንትና ኃላፊ ሚካኤል በርነር ከሚመራ የልዑካን ቡድን ጋር በዓለም አቀፍ የዲጂታል የፋይናንስ አገልግሎቶች ላይ አዳዲስ የትብብር ዕድሎችን ለመፈተሽ የሚያስችል ውይይት አካሂደዋል።
ቴሌብር ከቪዛ ዓለም አቀፍ ኔትወርክ ጋር በመጣመር አዳዲስ ፈጠራ የታከለባቸው የዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎቶች ማቅረብ የሚቻልበት ዕድሎች መኖሩን አብራርተዋል።
የቪዛ ኢንክ የልዑካን ቡድን በጋራ ተግባራዊ የተደረጉት ዓለም አቀፍ አገልግሎቶች ስኬት በማድነቅ የገበያውን ከፍተኛ ጥቅም ላይ ያልዋለ አቅም መጠቀም እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተዋል።
የትብብር ዕድሎችን በመፈተሽ የፋይናንስ ተደራሽነትን የሚያሰፋና በኢትዮጵያ የዲጂታል ፋይናንስ ባህል ግንባታ ላይ ጉልህ አሻራ ለማኖር ተቀራርቦ የሚሰራ የጋራ ቡድን ለማቋቋም መስማማታቸውን ከኢትዮ ቴሌኮም ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።