በምገባ ማዕከላት የሚጠቀሙ ዜጎች ከተረጂነት ወደ እራስን መቻል እንዲሸጋገሩ ጥረት እየተደረገ ነው

You are currently viewing በምገባ ማዕከላት የሚጠቀሙ ዜጎች ከተረጂነት ወደ እራስን መቻል እንዲሸጋገሩ ጥረት እየተደረገ ነው

AMN-ሚያዝያ 16/2017 ዓ.ም

የተስፋ ብርሃን ምገባ ማዕከላት ተጠቃሚዎችን በስራ ፈጠራ ተጠቃሚ ማድረግ ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራ እንደሚገኝ ተገለጸ።

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ቡዜና አልከድር መንግስት ለሴቶች መልካም እድሎችን በመፍጠር አበረታች ውጤት ተገኝቷል ብለዋል።

የተፈጠረው የስራ ዕድል ሴቶች ከተረጂነት ወደ አምራችነተ እንዲሸጋገሩ የሚያስችል መሆኑን ገልጸዋል።

ዜጎች ባገኙት ዕድል ከራሳቸው አልፈው ሌሎችን ወደ መርዳት ሊሸጋገሩ እንደሚገባም አሳስበዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሴቶች ሕጻናት እና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ቆንጂት ደበላ የዜጎችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በርካታ ሰው ተኮር ስራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ፤ ከነዚህ ተግባራት ውስጥ የምገባ ማዕከላትን ማስፋፋት ይጠቀሳል ብለዋል።

በ2016 ዓ.ም 100 ሴቶችን በማቋቋም የተጀመረው ስራው አበረታች ውጤት እየተገኘበት መሆኑ ሲገለጽ እነዚህ ዜጎች ሁሉም ስራ ላይ መሆናቸውን እና አንዳዶች ስራውን አሰፋፍተው እየሰሩ መሆኑን ብሎም ቁጠባ መጀመራቸው በክትትልና ድጋፍ መረጋጋጡን ኃላፊዋ ገልጸዋል።

በ2017 ዓ.ም 316 ተመልማዮችም ወደ ስራ እንደሚገቡ ሃላፊዋ አያይዘው ተናግረዋል፡፡

የእድሉ ተጠቃሚ የሆኑ ዜጎች ቀለል ባሉ የስራ ዕድሎች እንዲሰማሩ ስልጠና እንዲያገኙ መደረጉም ተመላክቷል።

በዚህም መሠረት በባልትና ስራ፣ በእንጀራ ጋግሮ መሸጥ፣ በችርቻሮ ንግድ፣ በዳቦ መጋገር እንዱሁም በችብስ ማምረትና መሸጥ ላይ የሚሰማሩ እንደሆነም ተገልጿል።

ይህ የሚጀምሩት ስራ ለቀጣይ ጥሪት ማፍሪያነት የሚያግዛቸውና በሂደት ስራቸውን አስፋፍተው በኢንተርፕራይዝ እንዲደራጁ የሚያስችላቸው መሆኑንም ወይዘሮ ቆንጂት ተናግረዋል።

በሀብታሙ ሙለታ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review